የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ ዛሬ ባደረገው አስቸካይ ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው ማንሳቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ ዛሬ ባደረገው አስቸካይ ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው ማንሳቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
(ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ሐረሪ ብሔራዊ ሊግ አመራሮች ለ 27 አመታት በክልሉ በሚኖሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት ጭቆና እንዲቆም በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ ቁጥራቸው ከ 600 በላይ የሚሆኑ የብሔረሰብ አባላት ባደረጉት አስቸካይ ስብሰባ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ እንደማይወክላቸው በሙሉ ድምጽ ገልጸው ነበር። የቀድሞውን የፖርቲው ሊቀ-መንበር የነበሩት እና ከድርጅት ተባረው የነበሩት አቶ ዘይዳን በክሪ የግዜያዊ ባላደራ ኮሚቴ ሰብሳቢ በማድረግ እንዲሰሩ ሲመደብ፣ ሌሎች 20 የኮሚቴ አባላት ሆነው እንዲሰሩ ተመርጠው ነበር።
ዛሬ ደግሞ የሊጉ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ሃረርን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

The post የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ ዛሬ ባደረገው አስቸካይ ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው ማንሳቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። appeared first on ESAT Amharic.


Source: esat