በአፋር በሰመራ ዪኒቨርስቲ የሰው ሃይል አደረጃጀት ሃላፊ ታፍነው መወሰዳቸው ተነገረ

አባይ ሚዲያ ዜና

የሰመራ ዩኒቨርስቲ የሰው ሃይል አደረጃጀት ሃላፊ ታፍነው መወሰዳቻው እና ያሉበት ቦታ እንደማይታወቅ ተዘገበ።

በዩኒቨርስቲው በሰው ሃይል አደረጃጀት ሃላፊነት ቦታ ላይ ይገኙ የነበሩት ግለሰብ በአገዛዙ የደህንነት አካላት ሳይታፈኑ እንደማይቀር አንድ የዩኒቨርስቲው መምህር ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

በክልሉ በሚገኘው በሰመራ ዩኒቨርስቲ ከቀናት በፊት የተቀሰቀሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ ሰዎች እየታሰሩ እና እየታፈኑ መሆናቸው ተነግሯል።

በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ወጣቶች አገዛዙን በመቃወም የሚያረጉት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ወደ አመጽ እየተለወጠ መምጣቱንም ተዘገቧል።

ከወጣቶቹ ጋር ውይይት ከማድረግ ይልቅ አገዛዙ የሃይል እርምጃዎች እንዲሁም እስራትን እየፈጸመ እንደሆነም ነዋሪዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

በአፋር ክልል የተቀሰቀሰው የህዝብ ተቃውሞ ከሰመራ ዩኒቨርስቲ አልፎ ከሰላሳ በላይ ወደ ሚጠጉ ወረዳዎች እየተስፋፋ በመሄዱ ምክንያት የመብት ጥሰቶች እየተፈጽሙ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።


Source: abbaymedia