የአባይ ወንዝ ህዳሴ ግድብ ትርፎች፤ ቦንድ፣ ዕዳ፣ አፈር መዛቅ፣ የጦር ዛቻ – በዘውገ ፋንታ

“የለም፣ አባይማ ይገደብ” በሚል አርዕስት ስለ አባይ ወንዝ ግድብ መቶ አለቃ አያልሰው ደሴ የሰጡትን አስተያየት አንብቤዋለሁ። ለዚህ
ጽሑፍ መነሻ የሆነው በዚያ የተሰጠው አስተያየት ነው። መቶ አለቃ አያልሰው ደሴ በክብር የሚጠሩ ኢትዮጵያ ካለቻቸው አንዱ ጀግና ሰው
ናቸው። አገራቸውን ያገለገሉና ጀብድነታቸው ጎልቶ የሚነገር መሆኑን፣ ሻለቃ ጌታቸው የሮም “ስም ከመቃብር በላይ” የተባለውን መጽሐፍ
ለሳቸውና ሌሎች መታሰቢያ ማድረጋቸው አንዱ ታላቅ ምስክር ነው። ስለዚህ ከዚህ በታች ያለው አጭር አስተያየት ይኽን ክብራቸውን
በመጠበቅ ነው። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ.