ሰይፈ ነበልባል – በ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ሰይፈ ነበልባል flameክርስትና እና ጋዜጠኝነት ሲወሀዱ ወደ ሰይፈ ነበልባልነት ይለወጣሉ። የክርስትናና የጋዜጠኝነት ሊቃውንት እንደሚያስቀምጡት “የክርስትና እና የጆርናሊዝም ውህደት በሰዎች ላይ  ሲከሰት ብልጭ ብሎ የማይጠፋ ፤ ህዝቡን ተብትቦ ያሰረውን ማእሰረ ፍዳ ለመበጣጠስ እንደ መብረቅ የተንቀለቀለ ሰይፈ ነበልባል ቦግ ይላል” ይሉና፤ ከውስጣቸው የሚፈልቀውን የውህደት ኃይል መግለጽ የሚችል የቋንቋ ቃላት ስለሚያጥር “መቃተት ነው” ይላሉ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

One Reply to “ሰይፈ ነበልባል – በ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ”

 1. አባታችን ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፣ እውነት እንደ እርስዎ አይነት አባት አለን? እድሜዎን ያርዝምንልን። ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን በሐሰት ተናጋሪዎች፣ በአድር ባዮች ጩኸት የተነሳ መንምና፣ ክብሯ ዝቅ ብሎ ትገኛለች። እንደርስዎ ያለ አባት ሲገኝ ደግሞ ይበርቱ ይበርቱ እንላለን። ፈተናው ከባድ ዘመኑ አስከፊ ነው። አቶ አዲሱ አበበም እንደዚህ መሆኑን አላወቅንም ነበር። አሁን ሁሉም ግልጽ ሆነ።ይህችንም ግጥም ያየነውን ለመመስከር ያህል አቅርበናል።

  ጋዜጠኛ

  እንዲህም አድርጎ የለ ጋዜጠኛ፣ የሐሰት መልእክተኛ፤
  ትዕቢተኛ የወንድ ትምክሕተኛ የጠብ መጫኛ ጌኛ።
  ክህደትን አበሳሪ የሐሰት ነጋድራስ የዋሾች መሪ፤
  ጠብ አጫሪ ጠብ አጫሪ…….።
  እውነትን የቀበረ የውሸት ዳኛ፤
  ቆርጦ ቀጣይ ሞገደኛ፤
  ይሄ ነው እንዴ ጋዜጠኛ?
  ከኔ በላይ ያወቀ
  ማን አለ የረቀቀ፤
  እያለ የሚመጻደቅ፤
  ይሄ ነው እንዴ ጋዜጠኛ እውቅ?
  ለእውነት የቆማችሁ ጋዜጠኞች፤
  የምትሉ ነን ለሕዝብ ተሟጋቾች፤
  ተነሱ ጠይቁት አዲሱ አበበን ፣ አምጣ በሉት መረጃ፤
  ለወያኔ ፊት ያቀረበውን መስገጃ።
  ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ፣ ምዕመንን ለመበተን ፤
  ሲራወጥ ቀን ከሌት የታለ የያዘው እውነትን?
  አይ ኢትዮጵያ አገራችን ያልታደልሽ፤
  እጅሸ አመድ አፋሽ የሆነብሽ፤
  እንዲህ አይነቱ አድር ባይ ነው የገደለሽ፤
  እውነተኛውማ ወጥቶ ቀረልሽ፥ ቀረብሽ፤
  አፈር በላልሽ ፥ ደመ ከልብ ሆነልሽ ፥ ሆነብሽ…….።
  እንዳወናበደ እድሜ ልኩን፤
  የማታ የማታ እውነት ያዘችው እጁን፤
  ጠለፈችው እግሩን ፣ አነቀችው አንገቱን ።
  እንግዲህ ቢያማትብ ቢል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤
  ቢማጠን እመቤቴን ድረሽልኝ አለዛሬም አልቀጥፍ አላፈርስ፤
  ቢደግም አሥር ውዳሴ ማርያም፤
  እውነት አለችው ወግድ ከአጠገቤ አንተ አድር ባይ ውሸታም።
  አበው እንዳሉት ሁሉም የዘራውን ያጭዳል፤
  በሰፈረው ቁና ይሰፈራል ፤
  በማሰው ጉድጓድ ይገባባታል።
  አሁንም እውነት ጩኺ፣ የነእስክንድር ነጋን የነርዕዮት ዓለሙን እንባ ሰቆቃ አብሺ፤
  እንደነአዲሱ አበበ ፥ ሄኖክ ሰማ እግዜር ያሉትን ከጎሬአቸው አጋልጪ ፊት ንሺ፤
  አሁንም እውነት ፋናሽን አብሪ፤
  ለዘለዓለም ኑሪ ኑሪ ኑሪ……………… ።

Comments are closed.