አቶ አንዳርጋቸው ምን ነክቷቸው ይሄንን ሁሉ ምስጢር ተናገሩ…? – አቤ ቶክቻው

አንድ ወዳጄ ያላት ነገር ቀድሞውንም በ አ ዕምሮዬ ስትመላለስ ነበር፤ ሰውዬውን ምንም አልተናገሩም እያላችሁ መከራቸውን ልታበዙት ነው እንዴ… አለኝ። የምሩን ነው…

ሰለዚህ አቶ አንዳርጋቸው ምን ነክቷቸው ይሄንን ሁሉ ምስጢር ተናገሩ፤ ብለን ብንደነቅላቸው ሳይሻል አይቀርም…

በነገራችን ላይ ከለንደን ቤተሰቦቹን ለማየት ሲሄድ የታሰረው አበበን ያሰሩት በስመ ሞክሼ ነው ማለት ነው… አቶ አንዳርጋቸው አበበ የሚባል መተማ አካባቢ ሸፍቶ የነበረ ሰው ነበር ይላል፤ ኢቲቪ ደግሞ ዲያስፖራውን አበበ መኪና ተደግፎ የተነሳውን ፎቶ ያሳያል። ወይስ ለንድደን ወስጥ መተማ የሚባል መሸፈቻ ቦታ አለ… እነዚህ ሰዎች በዚህ አይነት እኔም ብሄድ ሌላም አበበ አገኘን በለው ሊያስሩኝ ይችላሉኮ… ሃሃ

የሆነው ሆኖ አቶ አንዳርጋቸው ይሄንን ሁሉ ምስጢር እንዴት ነገራቸው…

እንዴ፤ የኮምፒውተሩን ፓስዋርድ ሁላ ነገራቸውኮ… በዛ ላይ ደግሞ በኮምፒውተሩ ውስጥ ምንም መረጃ የለውም አላቸው፤ ውይ ምን ነካው…

እንዴ፤ አብዛኛውን የግንቦት ሰባት ሃላፊነት የተሸከምኩት እኔ ነኝ ብሎ አመነላቸውኮ… ስለዚህ ከዚህ በኋላ ግንቦት ሰባት እያሉ ማሰር እንዲያቆሙ እገረ መንግዱን ነገራቸው ማለት ነው…. ምነ ነካው…

እንዴ፤ ግንቦት ሰባትን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂው የሚያግዙ ብዙ ሰዎች አሉ አላቸውኮ… አንዳንዶቹ በአይቲ ፒኤችዲ ሁላ አላቸው አላቸው… እነ ዶከተር ታደሰ ባለፈው ግንቦት ሰባትን ወክለው መግለጫ ሲሰጡ የግንቦት ሰባት አባል ይሆናሉ ብሎ ማን ጠረጠረ… ይሄው አቶ አንዳርጋቸው አይደል እንዴ ጉዱን ያፈረጠረጠው… ኧረ ምን ነካው….

ከሁሉ የገረመችኝ የውሃ እቃዋ ናት አንዴ ወደዚ አንዴ ወደዛ እንዴ ብርት አንዴ ጥፍት ስትል ነበር፤ በሚቀጥለው ቀጥቅጠው ቀጥቅጠው አርፋ እንድድትቀመጥ ካላደርጓት በውነት እነርሱ ደህነነቶች አይደሉም!

ለማንኛውም እስቲ ይቺን ቪዲዮ ቀልብዎን አሰባስበው ድጋሚ ይስሟት አንዳንዱ ቦታ በሳቅ ያፈነዳዎታ፤ ለመሳሌ ፖሊሱ ዘጋቢ ሲተርክ፤

3:55 ላይ አለችልዎ፤

በሌላ በኩል አሸባሪው ድረጀት ራሱን ከጥቃት እንዴት እንደሚከላከል እና በተለያየ ሽፋን ወደ ሃገር ውስጥ የሚያደርጋቸው ስርገቶች… (ሃሃ ገጣሚ እና ኢሃዴግ መቼም ቃል አያልቅባቸውም፤ ስርገቶች ደስ ብላኛለች። (ስርገቶች ሲል ስዕሉ ላይ የሚያሳየው ቦንቦችን ነው.. ቦንቦችን የሚያሰረጉ ለማለት ነው…) እና ለዚህ የሚተባበሩ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የሚገኙ ቁልፍ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ዝርዝር መረጃ ሰጥቷል… ብሎ ካለ በኋላ አቶ አንዳርጋቸው የሰጠውን መልስ ሲሰሙ በሳቅ ይሞታሉ….

እነርሱ የሚያወሩት ስለ ፈንጂ እርሱ የሚያወራው ስለ አይቲ!

የሆነስ ሆነና አቶ አንዳርጋቸው ምን ነክቶት ይሄንን ሁሉ መረጃ ሰጣቸው… ”ለሳቅ ልተወው” ትክክለኛ ቦታዋ አሁን ነው…

One Reply to “አቶ አንዳርጋቸው ምን ነክቷቸው ይሄንን ሁሉ ምስጢር ተናገሩ…? – አቤ ቶክቻው”

Comments are closed.