ሃብታሙ አያሌውን አሰሩት

 የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው ሃብታሙ አያሌው በዛሬው እለት ታስሯል። አንድነት ፓርቲ ይህን በተመለከተ የገለጸው ነገር ባይኖርም፤ ፓርቲውን በመወከል በፓርላማ ውስጥ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ ባስተላለፉት መል እክት፤ “ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ አይቻላቸውም፡፡ እልፍ አህላፍ የነፃነት ሰዎች ይፈጠራሉ፡፡ ለነገሩ የሚታሰሩ ንፁሃን ታሳሪዎች ሳይሆን አሳሪዎ በከፍተኛ የህሊና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን መረዳት አሰቸጋሪ አይደለም፡፡” ብለዋል።

ሃብታሙ የሲቪክ ድርጅት የሆነው፤ የባለራዕይ ወጣቶች መስራች እና ሊቀ መንበር ነበር። ሆኖም የባለራዕይ ወጣቶ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ፤ በኢህ አዴግ በኩል የሚደርስበት ጫና በማየሉ ምክንያት፤ ባለራዕይ ወጣቶች ድርጅትን በመተው አንድነት ፓርቲን የተቀላቀለ ወጣት ነው። አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች በሚያደርግበት ወቅትም ከፊተኛው ረድፍ ከሚሰለፉት አስተባባሪዎች ውስጥ አንዱ ነው። አንድነት ፓርቲ በቅርቡ አዲስ አበባ አድርጎት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ፤ ሰልፉን በሚመራበት ወቅት… “እመነኝ…!” እያለ ያሰማ በነበረው ቀስቃሽ መፈክሮቹ በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል። (ኢ.ኤም.ኤፍ)

One Reply to “ሃብታሙ አያሌውን አሰሩት”

Comments are closed.