Day: June 14, 2018

ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ ያሉ እውነታዎች

የህወሃት መግለጫ በመስመሮች መካከል ሲነበብ በተቀማ ጩኸት ሊመሰል ይችላል። ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ የነበሩ እውነታዎችን ለመዳሰስ የፖለቲካ ሊቅ መሆንን አይጠይቅም።ህወሃቶች አብረው ወስነው ያስተላለፉትን ጉዳይ እንደመጋዣ አኝከው ሲያበቁ፤ ከብዙ ገጽ የክስ ቻርጅ ጋር ብቅ ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማስጠቆር የሄዱበት ርቀት ግልጽ እና መሳጭ ነው። ሰማይ ወጥተው ቁልቁል ቢወርዱም ግን ከቶውንም የህዝብ ቀልብ

“ጄኔራል” አደም መሐመድ፤ ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት እስከ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተርነት

ወሎ-አምባሰል የተወለደው አደም መሐመድ በ1975 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ነባር ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በዋናነት የአዲሱ ለገሰ ሬዲዮ ኦፕሬተር ሆኖ ሰርቷል። አንዳንዶች በሰውየው ላይ ሲቀልዱ “የአዲሱ ለገሰ ሻሂ አፍይ” ይሉት ነበር። አደም መሐመድ ለአዲሱ ለገሰ ለአምልኮ የቀረበ ፍቅር ያለው በመሆኑ በሬዲዮ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በጽሁፍ ከመገልበጥና መረጃዎችን ከማድረስ ባሻገር ለሰውየው ማሸርገድ

ከኢትዮጵያ መንግስጥ የተሰጠ መግለጫ – የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ እና አገራዊ ድባብ ጠብቆ ማስቀጠል የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆን አለበት::

በአሁኑ ጊዜ በአገራችን እየሰፈነ ያለው ሰላምና መረጋጋት ብሎም እየታየ ያለው አገራዊ መግባባትና የህዝቦች አንድነት የአገራችንን ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በአፍሪካ ደረጃ ብሎም በዓለም አቀፍ መድረኮች ውጤት እያስገኘ ያለ ስኬት ነው። በዚህም የአገራችንን ብቻ ሳይሆን የምንገኝበትን የአፍሪካ ቀንድ እና የአካባቢውን ወቅታዊ ሁኔታ ከመሰረቱ የሚለውጥ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናችን ይታወቃል። በዚህም ዓለምን ያስደመመ

የአለም ዋንጫ በሩሲያ ሞስኮ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) 21ኛው የአለም ዋንጫ ዛሬ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ተጀመረ። በአለም ዙሪያ በቢሊየን የሚቆጠሩ ተመልካቾችን በመሳብ ግንባር ቀደም ሆኖ የተገኘው የአለም የእግር ኳስ ዋንጫ ከአፍሪካ የሚሳተፉ 5 ቡድኖችን ጨምሮ 32 ሀገራት ተሳታፊ ሆነውበታል። ከዛሬ ሰኔ 7/2010 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2010 የሚቆየው የአለም ዋንጫ በሩሲያ ሞስኮና ፒትስበርግን ጨምሮ በ11 ከተሞች

የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ቅሬታውን አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ላይ ቅሬታውን አቀረበ። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባድመን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሁም ግዙፍ የመንግስት ተቋማት በከፊል ወደ ግል እንዲዞሩ የተደረሰበትን ስምምነት ግን እንደሚቀበለው አረጋግጧል። የእስከዛሬው ድላችንም ሆነ የነገው ስኬታችን በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ብቻ ነው ብሏል የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ።

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ወጡ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው በመውጣት ላይ መሆናቸው ተገለጸ። የአማራ ተወላጆች የሚደርስባቸው ጥቃት እንዲቆም በመጠየቅ ባለፉት አራት ቀናት የተጀመረው ተቃውሞ በክልሉ ልዩ ሃይል የሃይል ርምጃ መወሰዱን ተከትሎ ተማሪዎቹ ሻንጣቸውን ይዘው ከግቢ መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ትላንት ግቢው ድረስ ዘልቆ የገባው ልዩ ሃይል በተማሪዎች ላይ ድብደባ በመፈጸም ከባድ

በጌዲዮ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ቀጥሏል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጅ በጌዲዮ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል መቀጠሉ እንዳሳሰበው በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የጌዲዮ ማህበረሰብ ማህበር አስታወቀ። ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ለሚመለከታቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ባለፈው 10 ቀናት ብቻ ከ2 መቶ በላይ የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ሲገደሉ ከ3መቶ ሺህ

በወልቂጤ ህዝባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) በወልቂጤ ህዝቡ ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ። የመከላከያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ ወጣቱን በማፈስ እያሰሩ ቢሆንም ነዋሪው ቁጣውን በመግለጽ ላይ ነው። በእስከሁኑ ተቃውሞም ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ የህክምና ማዕከላት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ከ30 በላይ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን አራት የመንግስት ተሽከርካሪዎችም በእሳት መጋየታቸው

በሃዋሳ በድጋሜ ግጭት ተነሳ

በሃዋሳ በድጋሜ ግጭት ተነሳ (ኢሳት ዜና ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም) በአመታዊው የሲዳማ የዘመን መለወጫ በአል -ጨምበለላ ቀን የተጀመረው ግጭት ዛሬ በድጋሜ ማገርሸቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የዛሬው ግጭት-ሁለት ሰዎች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸውን ተከትሎ የተነሳ ነው። የጨምበለላን በአል ወደ ብሄር ግጭት ለመቀየር የሚደረገውን ሙከራ ለማስቆም የአገር ሽማግሌዎች አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።

ህወሃት- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በባድመና የመንግስት ኢኮኖሚ ተቋማት ዙሪያ የወሰናቸውን ውሳኔዎች እንደሚቀበል አስታወቀ

ህወሃት- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በባድመና የመንግስት ኢኮኖሚ ተቋማት ዙሪያ የወሰናቸውን ውሳኔዎች እንደሚቀበል አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባድመን ለኤርትራ የወሰነውን የአልጀርሱን ስምምነት እንደሚቀበል እንዲሁም ዋና ዋና የሚባሉትን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም በሙሉ ወደ ግል ለማዞር የወሰነውን ውሳኔ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደሚቀበለው