Category: አማርኛ ዜና

ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለክቡር ዶር ዐቢይ አሕመድ፤ ስለ አፍሪካ ቀንድ ሕብረት ( በኪዳኔ ዓለማየሁ )

ክቡር ሆይ፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ምክር ቤት ያስተላለፉት መልእክት እንደዚሁም በቅርቡ ሶማልያ ያከናወኑት ታሪካዊ ጉብኝት፤ አሁን ደግሞ ፕሬዚዳንት ኢሣይያስ ስለ አልጂየርሱ ስምምነት መተግበር የሰጡት ቀና መልስ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም፤ ሕብረትና ልማት ያለኝን ከአሥር ዓመት በላይ የታገልኩበትን ዓላማና ተስፋ የሚያጠናክር ስለ መሰለኝ በትሕትና ላመሰግንዎ እወዳለሁ። ኢትዮጵያ፤ ኤርትራ፤ ጅቡቲና ሶማልያ አሁን ካሉበት ከመከፋፈል፤

የሃገርኛ ጀርመንኛ – እውን ኢህአዴግ አለወይ? ትርጉም ወደ አማርኛ ( መላኩ ከአትላንታ )

አሉላ ዮሃንስ የተባለ ሰው በትግራይ ኦንላይን ላይ እውን ኢህአዴግ አለወይ በሚል አርዕስት የከተባት ነገር ሳበችኝና ተመለከትኳት።ፅሁፏ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ከሆነች ፀሃፊውን ከአንገቴ ዝቅ ብዬ አድናቆቴን እገልፃለሁ።ከተሳካ ግሩም ሙከራ ነው።ነገር ግን አቶ አሉላ በእውን ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት ነበረ አሁን ግን የት ገባ ብሎ የፃፈውን የሚያምን ከሆነ ግን ትልቅ ችግር አለ። አንድ ላይ

በሃገራችን የዲሞክራሲ ለውጥ ለማምጣት ተገደን የገባንበትን ማንኛውንም ሰላማዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ ገተናል ( የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ልዩ መግለጫ )

June 22, 2018 የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት በርካታ አመታት ከአፈና አገዛዝ ለመላቀቅና ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ለመሸጋገር እልህ አስጨራሽ ትግል በማካሄድ ላይ ይገኛል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህዝባችን ትግል የወለደውና በኢህአዴግ ውስጥ ታፍኖ ይኖር የነበረው የለውጥ ሃይል ይህንን ትግል ተቀላቅሎ በዋነኛነት ትግሉን የመምራት ሃላፊነት እየተወጣ ነው። ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ከትናንት በስቲያ ሰኔ 13

የጣሊያን መንግስት ስደተኞችን የጫኑ ሁለት መርከቦችን አገደ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) የጣሊያን መንግስት ስደተኞችን የጫኑ ሁለት መርከቦችን በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸዋለሁ በሚል ማገዱን አስታወቀ። የጣሊያን መንግስት አግቻቸዋለሁ ያላቸው መርከቦች 226 ከአዳጋ የተረፉ ስደተኞችን ጭነው እንደነበርም ታውቋል። ከሊቢያ ወደብ የተነሱትንና አደጋ ላይ ወድቀው የነበሩትን ስደተኞች የጫኑት መርከቦች የሆላንድን ባንዲራ ሲያውለበልቡ እንደነበርም መረጃው አመልክቷል። በጣሊያን በቅርብ አዲስ የሀገር ውስጥ ጉዳይ

ኢሳትና ኦ ኤም ኤንን ጨምሮ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን በነጻነት እንዲታዩ ተፈቀደ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) ኢሳትና ኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥንን ጨምሮ በኢትዮጵያ ታግደው የነበሩ 264 ድረገጾች በኢትዮጵያ ውስጥ በነጻነት እንዲታዩ መፈቀዱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት የሌሎች ነጻነቶች መሰረት መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል። መንግስት በዚህ መነሻነትም የታገዱት ቴሌቪዥኖችና ድረገጾች እንዲከፈቱ ማድረጉን አመልክተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት

አርበኞች ግንቦት7 አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠቡን አስታወቀ

አርበኞች ግንቦት7 አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠቡን አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከሰኔ 15 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ አርበኞች ግንቦት 7 “በማናቸውም መልኩ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ምንም አይነት አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ ታቅቧል” ብሎአል። “ኢትዮጵያ ዉስጥ በየትኛዉም አካባቢ የሚገኙ የነጻነት ታጋዮቻችን ከማናቸውም የአመጽ እንቅስቃሴ

በቄለም ወለጋ ዞን የሚታዬው ውጥረት አለመቀነሱን የአማራ ተወላጆች ተናገሩ

በቄለም ወለጋ ዞን የሚታዬው ውጥረት አለመቀነሱን የአማራ ተወላጆች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በ1977 ዓም በነበረው ድርቅ ከወሎ ክፍለ ሃገር ተሰደው በቄለም ወለጋ መቻራ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶአደሮች ለኢሳት እንደተናገሩት ትናንት ከጠዋት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚሉ ወጣቶችና በእነሱ መካከል በነበረው ግጭት 11

የኤርፖርቶች ድርጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሸጥ አሳስቦኛል አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች በሽርክና ይተላለፋል መባሉ እንዳሳሰባቸው የኤርፖርቶች ድርጅት የቀድሞ ሰራተኞች ገለጹ። ሰራተኞቹ ስጋታቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በ2009 በጸደቀው አዋጅ መሰረት በመቀላቀሉ ነው። በየትኛውም ዓለም የኤርፖርቶች ድርጅት ከመንግስት ቁጥጥር ስር አይወጣም ሲሉም ያክላሉ። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ታላላቅ

ህወሃት የሰማዕታት ቀን በሚል የሚከበረውን በአል የተቃውሞ መገለጫ አድርጎት ዋለ

ህወሃት የሰማዕታት ቀን በሚል የሚከበረውን በአል የተቃውሞ መገለጫ አድርጎት ዋለ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ የትግራይ ሰማዕታት ቀን በሐውዜን ከተማ በተከበረበት እለት የተያዙት መፈክሮች ህወሃት በቅርቡ የኢትዮ- ኤርትራን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተቸት ያወጣውን መግለጫ የሚያንጸባርቁ ናቸው። የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ያልተሳተፉበት ሰላም ዘላዊ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሚካሄደው ሰልፉ ላይ ይገኛሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ነገ በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው ሰልፍ ላይ ይገኛሉ ተባለ። የሰልፉ አስተባባሪዎች በጠየቁት መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 በሚካሄደው ትዕይንተ ሕዝብ ላይ እንደሚገኙ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ለነገው ሰልፍ የሚደረገው ዝግጅት ቀጥሏል። ፌደራል ፖሊስ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ