Author: DireTribune

እኔና ደብዳቤዬ ለክቡር ጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

“ለእራት ሲያዘጋጁን ቁርስ አደረግናቸው” ( ኮ/ል መንግስቱ ሃ/ማርያም) ጠ/ሚ አቢይ አህመድ! ከግብፁ ሙርሲ ከተማሩ ከወያኔ አይሲሲዎች የሤራ ሽረባ ይድናሉ:: እርሶ የሚመሩት መንግስት ህዝባዊ አይደለም:: የእርሶን ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ውጥን የሚያፀድቀው ፓርላማ የህወሃት-ወያኔ ምልምሎች እንጂ የህዝብ ተወካዮች አይደሉም:: ‘ፋታና ጊዜ’ ለእርሶ መስጠቱ ችግር ሆኖ አይደለም ቅር የሚለን:: ሮም በአንድ ቀን ባትገነባም

የዚምባቡዌ ፖሊስ አዲስ ሃይል ሊያቋቁም ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010)የዚምባቡዌ ፖሊስ አዲስ ሃይል ሊያቋቁም መሆኑን አስታወቀ። አዲስ የሚቋቋመው ሃይል ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ ጾታና ከለርን ሳይለይ  ፈጣንና ሙያዊ በሆነ መልኩ ምላሽ የሚሰጥ ሃይል ነው። ይሄ ሃይል ቀደም ሲል የዜጎችን የሰብአዊ መብት በመጣስና የገዢዎችን እድሜ ለማራዘም አላግባብ የሆኑ ድርጊቶችን ይፈጽማል በሚል ሲወገዝበት የቆየውን ስሙን ይቀይረዋል ተብሏል። በዚምባቡዌ

የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጫ አቅጣጫ ለማሳት ያለመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአክቲቪስት ገዛህኝ ገብረመስቀል ግድያ ላይ ያወጣው መግለጫ ጉዳዮን አቅጣጫ ለማሳት የታለመ በመሆኑ እንደሚያወግዘው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ገለፀ:: የኮሚኒቲው ሰብሳቢ አቶ ታምሩ አበበ ለኢሳት እንደገለፁት የኤምባሲው መግለጫ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ እንደመጮህ የሚቆጠር ነው:: ኮሚኒቲው ይህን ያለው የአክቲቪስት ገዛህኝ ገብረመስቀልን ግድያ ለፖለቲካ ፍጆታ

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ተጠርጣሪዎችን በነጻ ያሰናበቱት ዳኛ ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኮማንድ ፖስት የተያዙ ተጠርጣሪዎችን በነጻ አሰናብተዋል የተባሉ ዳኛ መታሰራቸው ተሰማ። ዳኛው በሰጡት ውሳኔ ላይ የለመታሰር መብታቸው ተጥሶ ወደ ወህኒ መውረዳቸውም ታውቋል። ዳኛው ለሚመሩት ችሎት ተጠርጣሪዎቹን አቅርበዋል የተባሉት አቃቤ ሕግም ለአንድ ቀን ታስረው መለቀቃቸው ተሰምቷል። ግዳዩ የተፈጸመው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ደኖ ወረዳ ነው።ቀኑ ደግሞ ሚያዚያ

ኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን መብት በማክበር ረገድ 150ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) ኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን መብት በማክበር ረገድ ከአለም 180 ሀገራት ጋር ስትነጻጸር በ150ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ድንበር የለሽ የሪፖርተሮች ቡድን አመለከተ። ፋይል ድንበር የለሽ የሪፖርተሮች ቡድን የተባለ አለም አቀፍ ተቋም የየሃገራቱን የጋዜጠኞች መብት አከባበር አስመልክቶ ባወጣው የግምገማ ሪፖርት እንደገለጸው ኢትዮጵያ በአሸባሪነት ሰበብ ጋዜጠኞችን በማሳደድ የከፋ ርምጃ ትወስዳለች። ኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን

የአብዲ ዒሌና የሽንሌ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ድርድር ያለውጤት ተበተነ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) የአብዲ ዒሌና የሽንሌ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ድርድር ያለውጤት ተበተነ:: አንድ ሳምንት የሞላውን ተቃውሞ ለማስቆም በአብዲ ዒሌ በኩል ግፊት የተደረገበት ድርድር የከሸፈው በእስር ላይ የሚገኙ ወጣቶች እንደማይፈቱ በመገለፁ ነው:: የክልሉን ምክትል ፕሬዝዳንት የላከው አብዲ ዒሌ በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ በመሆናቸው ልንፈታቸው አንችልም የሚል መልስ ለሽማግሌዎቹ ተነግሯቸል :: ይህ በእንዲህ

የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእስር ከተፈቱት ታዋቂ ሰዎችና ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተነጋገሩ

የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእስር ከተፈቱት ታዋቂ ሰዎችና ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተነጋገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችና ጋዜጠኞች ጋር ተወያይተዋል። ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ዙሪያ እና

በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው

በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በረባራት እየተባሉ የሚጠሩ ወጣቶች በአቶ አብዲ ኢሌ አገዛዝ በመማረር የጀመሩትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። በርካታ ወጣቶች በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮች፣ የእስር ዘመቻው ተጠናክሮ በመቀጠሉ አካባቢው በውጥረት እንደሚሞላ አድርጎታል። ከፍተኛ

“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ

“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ይህን የተናገሩት በቤተመንግስት የመሸኛ ዝግጅት በተደረገላቸው ወቅት ነው። አቶ ሃይለማርያም ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያላቸውን አድናቆት ከገለጹ በሁዋላ በአገሪቱ እየነፈሰ ያለው የለውጥ ንፋስ ህዝቡ በሚፈልገው መሰረት እንዲከናወን ከፍተኛ ትግል ያስፈልጋል ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝርፊያ እየተፈጸመባቸው ነው

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝርፊያ እየተፈጸመባቸው ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢትዮጵያኑ እንዳሉት የአገሪቱ ዜጎች የፖለቲካ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ከወጡ በሁዋላ የስደተኞችን ንብረቶች በመዝረፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት፣ በዝርፊያው በርካታ ኢትዮጵያውያን ሃብትና ንብረታቸውን አጥተዋል። በሌላ በኩል ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች